ጋምቢያ የማይናማር መሪ ሳን ሱኪን ከሰሰች

13 Dec by Mihret Daniel

ጋምቢያ የማይናማር መሪ ሳን ሱኪን ከሰሰች

ጋምቢያ ሳን ሱኪ የሮሂንጊያ ሙስሊሞች ላይ በፈጸሙት የዘር ማጥፋት ወንጀል ሊጠየቁ ይገባል ስትል ለአለማቀፋ የፍትህ ፍ/ቤት አቤት ብላለች፡፡ የአለምን ህብረተሰብ አስጨብጭበዉ ፣የሰላም የኖቤል ሽልማትን የተቀበሉት ሳን ሱኪ በሀገራቸዉ ጉዳይ መልካም ስም የላቸዉም፡፡ በርካታ የሮሂንጊያ ሙስሊሞች በእርሳቸዉ አስተዳደር በሚዘዉር ታጣቂ ሃይል ለጥይት በአደባባይ ተመተዉ ወድቀዋል፤ለአካል ጉዳት ተዳርገዋል፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ሳን ሱኪ ግን ሰላምን ለማስከበር ነዉ […]
13 Dec by Mihret Daniel

እንግሊዝ እያካሄደች ባለችዉ ምርጫ ቦሪስ ጆንሰን የማሸነፍ እድላቸዉ የሰፋ መሆኑ ተነግሯል

ቦሪስ ጆንሰን ምርጫ እንዲደረግ ግፊት ሲያደርጉ የቆዩት ሀገሪቱ ከአዉሮፓ ህበረት የመነጠል ጉዳይን ለማሳካት በሚያደርጉት ጥረት በዙሪያቸዉ ደጋፊያቸዉን ለማብዛት እንዲያስችላቸዉ ነዉ በሚል ሲገለጽ ቆይቷል፡፡ ዋሸንግተን ፖስት ከደቂቃዎች በፊት ባወጣዉ ዘገባ ታዲያ ጆንሰን የማሸነፍ እድላቸዉ ከፍተኛ መሆኑን የሚያሳዩ መረጃዎችን አግኝቻለሁ ብሏል፡፡ 650 መቀመጫዎች ካሉት የእንግሊዝ ፓርላማ የቦሪስ ጆንሰን ወግ አጥባቂዎቹ ቢያንስ 368 መቀመጫዎችን ሊያገኙ እንደሚችሉ ጽፏል፡፡ይህም እ.ኤ.አ […]
12 Dec by Mihret Daniel

የ13 ዓመቷን ታዳጊ አስገድዶ የደፈረው ተከሳሽ ስምንት ዓመት በፅኑ እስራት ተቀጣ

በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የወንጀል ህግ አንቀፅ 624 /4/ ሀ እና አንቀፅ 628/ሀ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ የግብረ ስጋ ድፍረት ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በፅኑ እስራት መቀጣቱን በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ጠቅላይ አቃቤ ህግ የቂርቆስ ምድብ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡ ተከሳሽ አብነት ለገሰ በኤሌክትሪክ ስራ የሚተዳደር የ26 አመት ወጣት ሲሆን በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የወንጀል ህግ በአንቀፅ 624 /4/ ሀ እና በአንቀፅ […]
12 Dec by Mihret Daniel

የኢራንና ቻይና ባለሃብቶች በኢትዮጵያ የሂልኮፕተር አምቡላንስ ያላቸው ስፔሻላይዝድ ሆስፒታሎችን በመገንባት ላይ እንደሆኑ ተገለጸ

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን እንዳስታወቀዉ አለም አቀፍ ደረጃቸዉን የጠበቁ ሆስፒታሎች በዉጪ ባለሃበቶች ተገንብተዉ አገልግሎት ይሰጣሉ ብሏል፡፡ በኮሚሽኑ የፕሮጀክቶች ድጋፍና ክትትል ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል አሰፋ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት በቻይና እና በኢራን ባላሃብቶች የሚገነቡት እነዚህ ሆስፒታሎች፤አለም አቀፍ ደረጃቸዉን የጠበቁ እንደሚሆኑም ተነግሯል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ የቻይና ባለሃብቶች ሆስፒታል መገንበታቸዉን ያስታወቁት ዳይሬክተሩ በቅርቡም አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ብለዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም […]
12 Dec by Mihret Daniel

አስመጪና ላኪዎች በሚያቀርቡት የሀሰት የኪሳራ ሪፖርት መማረሩን የንግድና ኢንዱሰትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ

በኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ውስጥ የሀሰት የኪሳራ ሪፖርት አሳሳቢ መሆኑን የንግድ እና ኢንድስትሪ ሚስቴር ተናግሯል፡፡ ወደ ውጪ በሚላኩ ምርቶች ላይ ላኪዎች የውሸት የኪሳራ ኦዲት ሪፖርት በማዘጋጀት እና በማቅረብ ፣ መንግስት ህጋዊ ገቢ እንዳይሰበስብ ማድርጋቸው ተገልጿል። ድርጅቶቹ የሀገር ውስጥ የገበያ ዋጋ እንዳይረጋጋ ከማድረጋቸው በላይ ፣ ከዘርፉ የውጭ ምንዛሬ እንዳይገኝ አድርገዋል፡፡ የሀሰት የኪሳራ ሪፖርት በሚያዘጋጁና ለመንግስት በሚያቀርቡ ድርጅቶች […]
12 Dec by Mihret Daniel

እንግሊዛዊያን የ2019 አጠቃላይ ምርጫ እያካሄዱ ነው

በአምስት አመታት ውስጥ በ 2015 እና በ 2017 ከተደረገው ሶስተኛው የሆነውን አጠቃላይ ምርጫ ለማድረግ እንግሊዛውያን ወደ ምርጫ ጣቢያ አቅንተው እየመረጡ ነው፡፡ በእንግሊዛ በዌልስ በስኮትላንድና በሰሜን አየርላንድ በሚገኙ 650 የምርጫ ክልሎች የምርጫ ጣያዎች ለመራጮች ክፍት መሆናቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። ምርጫው ከተጠናቀቀ በኋላ ቆጠራው ወዲያው የሚጀምር ሲሆን ነገ ጠዋት ውጤቶች መገለፅ ይጀምራሉ ተብሏል፡፡ መራጮች ምርጫቸውን በሚጠቁሙበት the first-past-the-post […]
11 Dec by EthioFM

የ16 ዓመቷ ስዊድናዊት ጌሬታ ተንበርግ የታይም መፅሔትን የአመቱ ሰው ክብርን አሸነፈች

የ16 አመቷ ስዊድናዊት የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋች ግሬታ ተንበርግ የታይም መፅሔት የአመቱ ሰው ክብር ተቀዳጅታለች፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ፣ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ ከታጩት ውስጥ ነበሩ፡፡ በሔኖክ አስራትታህሳስ 1 ቀን 2012 ዓ.ም
11 Dec by EthioFM

የዘጠኝ ዓመቷን ህጻን አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ በዘጠኝ ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ

የ17 ዓመቱ ተከሳሽ ዳዊት አለማየሁ ባልቻ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀፅ 627 (1) ላይ የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ሰኔ 19 ቀን 2010 ዓ.ም በግምት ከምሽቱ12:00 ሰዓት አካባቢ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ “ጀምቡላ” እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የ9 ዓመቷን ህፃን ከምትጫወትበት ቦታ ብስኩት ልግዛልሽ በማለት አታሎ ከወሰዳት በኋላ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመ በመሆኑ በዐቃቤ ህግ […]
11 Dec by EthioFM

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለዘጠኝ የፖለቲካ ፓርቲዎች እውቅና ሰጠ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሚከተሉት በምዝገባ ሂደት ላይ የነበሩ ፓርቲዎች እውቅና መስጠቱን አስታውቋል። ቦርዱ እውቅና የሰጣቸውን የፖለቲካ ፓርቲዎችን ስም እንደሚከተለው ዘርዝሯል። 1. አፋር ህዝባዊ ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢህፍዴፓ)2. አፋር ህዝብ ነጻነት ፓርቲ (አህነፓ)3. ጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ጋዴፓ)4. ሞቻ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(ሞዴፓ)5. ቁማ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቁህዴፓ)6. ካፋ አረንጓዴ ፓርቲ (ካአፓ)7. ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ)8. ዎላይታ ብሔራዊ […]
11 Dec by EthioFM

በድሬዳዋ እና በኮምቦልቻ ከ7.7 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ እቃና ዶላር መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ

የገቢዎች ሚኒስቴር ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው በጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ከምሽት 3፡00 ሰዓት ከብር 7.7 ሚሊዬን በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ሥር ውሏል፡፡ በሰሌዳ ቁጥር 45074/14652 ኮንቴነር የጫነ ተሽከርካሪ ሀሰተኛ ሰነድ በመያዝ ወደ አዲስ አበባ በመጓጓዝ ላይ እያለ ደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ ሀርቡ ከተማ ላይ በክልሉ ፖሊስ አባላት […]