ማህበሩ በየዓመቱ በመቶ ሺህ ለሚቆጠሩ ሰዎች ድጋፍ አደርጋለሁ አለ፡፡  

(የካቲት 19 ቀን 2010 ዓ.ም)

 

ማህበሩ በየዓመቱ በመቶ ሺህ ለሚቆጠሩ ሰዎች ድጋፍ አደርጋለሁ አለ፡፡  

ይህን ያለው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ነው፡፡

በማህበሩ የሰብዓዊ ዲፕሎማሲያዊና የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ  ዶ/ር ሰለሞን አሊ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት በተለይ የውሃ እጥረት ባለባቸው አካባቢዎች ላሉ ነዋሪዎች የውሀ ጉድጓዶችን በማስቆፈር በቂና ንፅህናው የተጠበቀ ውሀ እንዲያገኙ ያደርጋሉ፡፡

ከተለያዩ ሀገራት ካሉ የቀይ መስቀልና የቀይ ጨረቃ ማህበራት ጋር በመተባበር በውሀና ንፅህና አጠባበቅ፤ ከበሽታ ወረርሽኖች መከላለከል፤ እንዲሁም ግድቦችንና አጠቃላይ የማህበረሰብ አቀፍ ስራዎችን በመስራት በአመት ለ 4 መቶ ሺህ ሰዎች መድረስ ችለናል ብለዋል፡፡

በሱማሌ፤ በቤኒሻንጉልና አፋር ክልሉች የተሰሩት መለስተኛ የመስኖና  ሌሎች ሰብዓዊ ድጋፎች ለዚህ ማሳያዎች ናቸው ብለውናል ዶክተር ሰለሞን፡፡

ወቅታዊ ያልሆኑ የአየር ንብረት ችግሮች ሲገጥምና አፋጣኝ የሰብአዊ ድጋፍ ሲያስፈልግ ከኦስትሪያ፤ ከቻይና፤ ኔዘር ላንድ፤ ፊላንድ፤ ካናዳና ስፔን ሀገራት ካሉ ቀይ መስቀል ድርጅቶች አፋጣኝ ድጋፍ እንደሚያደርጉላቸወም ነግረውናል፡፡

አሁን ደግሞ በቅርቡ ከኳታሩ ቀይ ጨረቃ ጋር የትብብር ስምምነት አድርገናል፡፡ ይህም የሰብዓዊ ድጋፎቻችንን በተጠናከረ መልኩ እንድንሰጥ የሚያስችለንን አቅም እናካብታለን ይላሉ ዶክተር ሰለሞን፡፡

የአባላት ቁጥር ከፍ ማለቱ ሌላው አጋዥ አቅም መሆኑንም ሀላፊው ነግረውናል፡፡ ላለፉት 2 እና 3 ዓመታት የአባላት ቁጥር 3 ሚሊየን የነበረ ሲሆን አሁን ግን ይህ ቁጥር ወደ 6.1 ሚሊዮን ከፍ ብሏል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ማህበሩ 44 ሺህ በጎ ፈቃደኞች አሉት፡፡

ዘገባው የደረሰ አማረ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *