የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጠቅላይ ሚንስትር ሀይለማርያም ደሳለኝን ከስልጣን መልቀቅ አደነቀ፡፡

(የካቲት 19 ቀን 2010 ዓ.ም)

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጠቅላይ ሚንስትር ሀይለማርያም ደሳለኝን ከስልጣን መልቀቅ አደነቀ፡፡

ድርጅቱ ውሳኔው በሀገሪቱ ለአስተዳደራዊ መሻሻልና ፖለቲካዊ ተሳትፎን ለማሳደግ ያግዛል ብሏል በመግለጫው፡፡

የተባሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝን ጠቅሶ የናይጀሪያው  ፕሪሚየም ታይምስ እንዳስነበበው ጠቅላይ ሚንስትሩ በገዛ ፈቃዳቸው ከስልጣን መልቀቃቸው  በኢትዮጵያ የፖለቲካ አስተሳሰብ ለውጦች እንዲመጡ መሰረት የሚጥል ነው፡፡

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ እና በአፍሪካ አህጉር በሰላም፣ በደህንነት፣ ልማትና ሰብአዊ መብት ጉዳዮች ላይ የተባበሩት መንግስታት ሁነኛ አጋር መሆኗን  ጉቴሬዝ ተናግረዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኢትዮጵያ አስተዳደራዊ መረጋጋትና ልማት እንዲሻሻል ድጋፍ ለማደረግ ዝግጁ መሆኑንም ዋና ጸሀፊው ገልጸዋል፡፡

አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ይህን ያሉት በቃል አቀባያቸው በኩል ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *