የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን እየገመገመ ነዉ፡፡

(የካቲት 19 ቀን 2010 ዓ.ም)

 

የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን እየገመገመ ነዉ፡፡

36ኛዉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተቋማዊ ለዉጥ ምክር ቤት ጉባኤ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አስተናጋጅነት ዛሬ ተጀምሯል፡፡፡

ጉባኤዉ በትምህርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት በየ 3 ወሩ የሚካሄድ ነዉ፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አሰማሀኝ አስረስ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ጉባኤዉ በዩኒቨርስቲዎች የተሰሩ ስራዎች የሚገመገሙበትና ተቋሞቹ ያሉበትን ደረጃ በመፈተሽ ድካምና ጥንካሬያቸዉን ለመለየት የሚያስችል ነዉ፡፡

በዚህ ጉባኤም የስድስት ወራት የስራ እንቅስቃሴን ከመፈተሽ ባሻገር፣የስነ-ዜጋና ስነ-ምግባር ትምህርቶች አሰጣጥና ፋይዳዉ እንዲሁም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዉስጥ የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭትና አጠቃላይ ያለበት ሁኔታ ላይ ያተኮሩ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበዉ ዉይይት ይደረግባቸዋል ብለዉናል፡፡

ጉባኤዉ ዩኒቨርስቲዎች ትልቅ የልምድ ልዉዉጥ የሚያደርጉበት፣ በጋራ ተደጋግፈዉ የሚሰሩበትን መድረክ የሚያጠናክሩበትና ለችግሮች የጋራ መፍትሄ የሚያስቀምጡበት መሆኑንም አቶ አሰማሃኝ ለባልደረባችን ሙሉቀን አሰፋ ነግረዉታል፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *