በመጪው እሁድ የሴቶች ብቻ ሩጫ ይካሄዳል::

0
205

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጲያ በየዓመቱ  የዓለም ዓቀፉ የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ ላለፉት 14 ዓመታት ‹‹ ቅድሚያ ለሴቶች ›› በሚል መርህ የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ  የሩጫ ውድድር ሲያካሂድ ቆይቷል ፡፡

ዘንድሮም ከተባበሩት መንግስታት በኢትዮጲያ ጋር በመተባበር ‹‹ ከጥቃት ነጻ ህይወት መብቴ ነው›› በሚል መርህ ውድድሩን ያደርጋል ፡፡

ለ15ኛ ጊዜ በሚደረገው በዚህ ውድድር 12ሺ ሴት የጤና ሯጮች ፣ ሁለት መቶ ሴት አትሌቶች እና 30 ተምሳሌት ሴቶች እንደሚሳተፉበት ተነግሯል ፡፡

ዜናውን የፃፈው አቤል ጀቤሳ

(የካቲት 30 ቀን 2010 ዓ.ም)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here