አሜሪካ በደቡብ ሱዳን ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ እንዲጣል ጠይቃለች፡፡

0
166

የተባበሩት መንግስታት የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት በደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ኃይላት ላይ የጦር መሳሪያ ማዕቀብ እንዲጥል አሜሪካ  ሰለመጠየቋ ተዘግቧል፡፡

አሜሪካ  ለምክር ቤቱ ባሠራጨችዉ ረቂቅ ዉሳኔ እንዳለችዉ የደቡብ ሱዳን ጦርነት ለማስቆም የተደረገዉን ሥምምነት ተግባራዊ በማያደርጉ ወገኖች ላይ ምክር ቤቱ አስፈላጊዉን እርምጃ መዉሰድ አለበት።

አምስተኛ ዓመቱን የያዘዉን የደቡብ ሱዳንን ጦርነት ለማስቆም ተፋላሚዎች ሶስት  ጊዜ የሠላም ስምምነት  ቢፈራረሙም አንዱም ሥምምነት አልተተገበረም፡፡

አሜሪካ  ለምክር ቤቱ አባል ሐገራት ዲፕሎማቶች ያሰራጨችዉ የዉሳኔ ሐሳብ የሰላም ዉሉን ይጥሳሉ በሚባሉ ወገኞች ላይ የጦር መሳሪያ ሽያጭ ማዕቀብን ጨምሮ የተለያዩ እርምጃዎችን እንዲወሰድባቸዉ የሚጠይቅ ነዉ።

ዲፖሎማቶች እንደሚሉት ተፋላሚ ኃይላትን የተኩስ አቁም ዉል ያፈራረመዉ የአፍሪቃ ሕብረት በጁባ በመንግሥት እና በአማፂያኑ ኃይላት ላይ የጦር መሳሪያ ሽያጭ ማዕቀብ ይጣል የሚለዉን ሐሳብ ይደግፋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here