ቢቢሲ እንዳወራው ጥሪው የቀረበው  ዋሽንግተን የሚገኘው  የደቡብ ኮሪያ ከፍተኛ ባለስልጣናት  ከሰሜን ኮሪያ  የተላከውን ደብዳቤ አቅርበዋል፡፡

እንደ ኃላፊዎቹ ከሆነ ኪም የኒውክለር ፕሮግራሙን  እስከ  መዝጋትም የሚያደርስ ቁርጠኝነት አሳይተዋል ብለዋል መልዕክተኞቹ፡፡

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራንምፕ የሰሜን ኮሪያ ባለስልጣናት ለኒውክለር ድርድር ያሳዩትን ፍላጎት አድንቀዋል፡፡
የደቡብ ኮሪያ ፕሬዝደንት ሙን ጃን ኢን  ውይይቱን የሰላም ድርድር ብለውታል፡፡

ይህ ከወራት ማስፈራሪያ እና እንቢተኝነት በኋላ የተገኘ ትልቅ እመርታ ነው ይላል የቢቢሲ ዘገባ።

ተንታኞች  ውይይቱ  ግን  ‘ያቻኮሉት ነገር  ምዕራፍ አያገኝም’  በማለት ጥርጣሬ እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡
ፕሬዝዳንት  ዶናልድ ትራምፕ  ትልቅ ስኬት  ቢሆንም  ማዕቀቦቹ ግን ተጨባጭ የሆነ ውጤት  ላይ እስኪደረስ ድረስ ባሉበት ይቀጥላሉ ሲሉ አሳስበዋል፡፡

ሰሜን ኮሪያ በዚህ ጎዳይ ላይ ትንፍሽ አላለችም፡፡

(ያይኔአበባ ሻምበል እንደጻፈችው)

የካቲት 30 ቀን 2010 ዓ.ም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here