የፖግባ ሰሞንኛ ችግር ምክንያት ተነገረ::

Written by on March 9, 2018

ፖል ፖግባ እያደረገ ባለው  እንቅስቃሴ ብዙዎች እየተተቸ ነው ፡፡ በ89 ሚሊዮን ፓውንድ የዝውውር ክፍያ ዩናይትድን የተቀላቀለው አማካይ ጎሎችን እያስቆጠረ አይደለም ፡፡ ጎል የሆኑ ኳሶችንም በሚጠበቀው ልክ አመቻችቶ እያቀበለ አይደለም ፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ የተሰጠው ሚና እና በዙሪያው ያሉ ተጫዋቾች መሆናቸውን ቢቢሲ አስነብቧል ፡፡

አሰልጣኝ ጆዜ ሞውሪንሆ ቡድናቸው ሚዛን እንዲኖረው አጥብቀው ይሻሉ ፡፡ በዚህ ምክንያት ገና 11ዱን የመጀመሪያ ተሰላፊዎቻቸውን እንኳን አልለዩም ፡፡

ዩናይትድ በርካታ ባለተሰጥኦ የፊት መስመር ተጫዋቾችን በመያዙ ፖግባ አፈግፍጎ እንዲጫወት ያደርጋሉ ፡፡ እስካሁንም ከአሌክሲስ ሳንቼዝ ጋር የተሳካ ጥምረት አልፈጠሩም ፡፡

አሌክሲስ ሳንቼዝ ዩናይትድን ከመቀላቀሉ በፊት ፖግባ ሜዳ ላይ ከቆየባቸው ደቂቃዎች አንጻር ጎል የሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ በማቀበል በአውሮፓ አምስቱ ታላላቅ ሊጎች ከሚጫወቱ ተጫዋቾች  ቀዳሚው ነበር ፡፡

በየ126 ደቂቃዎች ጎል የሆኑ ኳሶችን ያቀብል ነበር ፡፡ ሳንቼዝ ከመጣ በኋላ ግን አንድም ጎል የሆነ ኳስ አላመቻቸም ፡፡

ዜናውን የፃፈው አቤል ጀቤሳ

(የካቲት 30 ቀን 2010 ዓ.ም)


Reader's opinions

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *


LIVE – የቀጥታ ስርጭት

Ethio FM Radio Live

Current track
TITLE
ARTIST