የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ዶክተር አብይ አህመድ የኢህዴግ ሊቀመንር ሆነው መመረጣቸው መልካም ነው አሉ፡፡

የኢህአዴግ ምክር ቤት ባደረገው ስብሰባ ግንባሩን በሊቀመንበርነት እንዲመሩለት ዶክተር አብይ አህመድን በመምረጥ ማጠናቀቁ ይታወቃል        ፡፡

በዚህም መሰረት ዶክተር አብይ አህመድ የድርጂቱ አሰራር በሚፈቅደው መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትር እንደሚሆኑ ይጠበቃል፡፡

ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ኢትዮ ኤፍ ኤም የተለያዩ የፓለቲካ ፓርቲ አመራሮችን  አነጋግሯል፡፡

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ ለጣቢያችን እንዳሉት ዶክተር አብይ ቀደም ሲል በተለይ ከወጣቶች ጋር ሲሰሩ ነበር፤ በህዝቡ ውስጥ ያለውንም ችግርም ጠንቅቀው ያውቁታልና ለቦታውም ትክክለኛ ሰው ናቸው፡፡

አሁን ላለው ሆኔታ ከዚህ የተሻለ መፍትሔ የለውም ጥሩ ምላሽ ነው ያሉት አቶ በቀለ ይሁንና ብዙ ፈተናዎች አሉባቸው ከዚህም መካከል የፓለቲካ ምህዳሩን ማስፋት የመጀመሪያው ነው ብለዋል፡፡

ኢህአዲግ የተጀመረውን ሰዎችን የመፍታቱን ስራ በእርሳቸው የስልጣን ዘመን የሚቀጥል ከሁነ የተሻለ ለውት ይመጣል ሲሉም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
እኔ በእርሳቸው መመረጥ ደስተኛ ነኝ፡፡እርሳቸው ከሚወክሉት ፓርቲ በተለየ ጥሩ እይታና አቋም ያላቸው ሰው ናቸው ያሉን ደግሞ  የኤዴፓ መስራችና አባል አቶ ልደቱ አያሌው ናቸው፡፡

ዶክተር አብይ በእድሜ ወጣት በትምህርትና በስራ ልምዳቸውም ጥሩ በመሆናቸው ትንሽ ተስፋ እንዲታየኝ አድርጎኛል፤እኛም ብንሆን  ልንደግፋቸው ይገባል ነው ያሉት አቶ ልደቱ፡፡

በመድረክ ምክትል ሊቀ መንበርና የውጭ ጉዳይ ሃላፊ እንዲሁም በኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ ሰብሳቢ የሆኑት ፕሮፌሰር በየነ ጲጥሮስ ደግሞ በኢሀዲግ አስራር  መሰረት  ዶክተር አብይ እንሚመረጡ ቀደም ሲልም ይገመት ነበር በተለያየ ሁኔታ የሚዲያው አካል አድርጓቸው  ነበር ይላሉ፡፡

እርግጥ ደክተር አብይ የግል አቋም መልካም ይሁን እንጂ በኢሀዲግ አሰራር ውስጥ ያለው ትግል ከባድ ይሆንባቸዋል ብዬ አስባለሁ ብዋል ፕሮፌሰር በየነ፡፡

የእርሳቸወን መመረጥ በበጎ ነው የምናየው ያሉት የመላው ኢትዩጲያ አንድነት  ሊቀመንበር አቶ ሙሉጌታ አበበ  ኢህአዲግ የወሰደው እርምጃ ጥሩ ነው ዶክተር አብይ  ግን ከፍተኛ የቤት ስራ ይጠብቃቸዋል ብለዋል፡፡

ኤትዩ ኤፍ ኤም ያናገራቸው የፓርቲ አመራሮችና አባላት  ለዶክተር አብይ አህመድ ቀጣዩ የስራ ዘመናቸው የተሳካ ይሆንላቸው ዘንድ መልካም ምኞታቸውን ገልጸውላቸዋል፡፡

ያይኔአበባ ሻምበል እንደዘገበችው፡፡
(መጋቢት 20/2010 ዓ.ም)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *