የሂዝቦላ የምርጫ ውጤት እስራኤልን አስቆጥቷል፡፡

ሊባኖስ ባካሄደችው የፓርላማ ምርጫ አሜሪካና አጋሮቿ አሸባሪ ብለው የሚጠሩትና በኢራን የሚደገፈው ሂዝቦላህ በርካታ ወንበሮችን አግኝቷል፡፡

የሂዝቦላህ መሪ የሆኑት ሰይድ ሀሰን ነስረላህ  ይህ ለድርጅታችን ፖለቲካዊ ብቻ ሳይሆን በሞራልም ትልቅ ጥንካሬን የሚሰጠንና ትርጉም ያለው ድል ነው ብለዋል፡፡

ሚድል ኢስት ሞኒተር እንዘገበው የእስራኤል ባለስልጣናት ይህ የምርጫ ውጤት የሚያሳየው ሊባኖስን ከአሸባሪው ሂዝቦላህ ለይቶ ማየት እንደማይቻል ነው ብለዋል፡፡

በምእራባዊያን የሚደገፉት የሊባኖሱ ጠቅላይ ሚንስትር ሰይድ ሀሪሪ ፓርቲ ብዙ መቀመጫዎችን በምርጫው ተሸንፏል ተብሏል፡፡ ለዚህ ደግሞ አዲሱን የሀገሪቱን የምርጫ ህግ አውግዘዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *