ደቡብ ኮሪያ፣ጃፓንና ሰሜን ኮሪያን ችግሮቻቸዉን በዉይይት ፍቱ እያለች ነው፡፡

የደቡብ ኮሪያዉ ፕሬዝዳንት ሙንጃ-ኢን እንዳሉት፣ድንበርን አጥሮ መቀመጥ ማንንም ተጠቃሚ አያደርግም፡፡ እናም ሁለቱ ሀገራት በመነጋገር ግንኙነታቸዉን ማሻሻል ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

የሁለቱ ሀገሮች ግንኙነት መሻሻል በኮሪያ ልሳነ-ምድር ብቻም ሳይሆን፣ በሰሜን ምስራቅ እስያም ጭምር ሰላምና መረጋጋትን ይፈጥራል ነዉ ያሉት፡፡

ፕሬዝዳንት ሙንጃ-ኢን ሀገራቸዉ ከሰሜን ኮሪያ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሻሻል እንደሚሰሩ ጠቁመዉ ሌሎች ሀገራትም ለሰላም ትብብር ቅድሚያ ሰጥተዉ እንዲሰሩ ማሳሰባቸዉን ፐሬስ ቲቪ ዘግቧል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *