ሳተላይቶች ህገወጥ የደን ጭፍጨፋን ለመቆጣጠር ጥቅም ላይ መዋላቸዉ ተሰምቷል፡፡

0
205

ለአደጋ የተጋለጡ ዝናባማ ደኖችን ለመቆጣጠር ሳተላይቶች ‹የሰማይ ላይ የደህንነት ካሜራዎች እየሆኑ መምጣታቸውን ስካይ ኒውስ ጽፏል፡፡
የደቡብ አሜሪካው አማዞን ደን የሚያካልለውን የጓቴማላ ደን፣ ከህገወጥ ደን ጨፍጫፊዎች  በስኮትላንድ ዋና ከተማ ኤዲን-በርግ አቅራቢያ የተቋቋመው የመቆጣጠሪያ ጣቢያ፣ ተከታታይ የፎቶግራፍ ቅኝት በማድረግ የሚቆረጡ ዛፎችን መከላከል እንደተቻለ ባለሙያዎቹ ተናግረዋል፡፡

በጥ-ብቅ ደን ውስጥ ገብተው ዛፍ የሚቆርጡ ህገወጦች ከተገኙ፣ በተዘረጋው የግንኙነት መስመር መሠረት በጥበቃ ላይ ለሚገኙ ፖሊሶች ወዲያዉኑ በማሳወቅ እርምጃ እንዲወሰድባቸዉ ለማድረግ ያስችላል ተብሏል፡፡
ጓቴማላ ካላት የቆዳ ስፋት ሲሶ ያህሉ በደን የተሸፈነ ቢሆንም፣ ከዚህ ውስጥ አንድ ከመቶ ያህሉ በየዓመቱ በአደገኛ እጽ አብቃዮች ይጨፈጨፋል ፡፡
ለዕጹ ማብቀያነት ከሚውለው መሬት ውጭ፣ ምርቱን ለሚያጓጉዙ አነስተኛ አውሮፕላኖች ማኮብኮቢያነት ይውላል፡፡ አርሶአደሮችም ቢሆኑ የከብቶቻቸውን የግጦሽ ክልል ለማስፋት ዛፎችን ይቆርጣሉ፡፡ እነዚህን ሁሉ ችግሮች ለመፍታት  ሳተላይቶች ከፍተኛ ጥቅም እየሰጡ ነዉ ብሏል ዘገባዉ፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here