ሱዳን የጎረቤቷ ጉዳይ ያሳሰባት ትመስላች፡፡

ካርቱም በሁለቱ ደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ሀይለሎች መካከል እርቅ እዲወርድ የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ማሰቧን ተናግራለች፡፡

የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር ሀሰን አል በሽር የደቡብ ሱዳኑ አቻቸው ሳልቫ ኪርና ተቀናቃኛቸው ኤሪክ ማቻር ተገናኝተው በሰላም ዙሪያ እንዲወያዩ መድረክ ለማመቻቸት እቅድ ይዘዋል፡፡

ሲጂቲኤን እንደዘገበው ሳልቫ ኪር የአልበሽርን ሀሳብ አድንቀውታል፡፡ ሱዳን ይህን ሀሳብ ያቀረበቸው በትናንትናው እለት ከፍተኛ ባለስልጣኖቿ ለስራ ጉብኝት ጁባ በተገኙበት ወቅት ነው፡፡

አልበሽር ለደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር በላኩት መልእክት ሀገራቸው ሁለቱን ወገኖች ወደ ሰላም ለማምጣት ምንጊዜም ዝግጁ ናት ብለዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *