ሁለቱ መሪዎች በሲንጋፖር ተገናኝተው ተወያይተዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕና የሰሜን ኮሪያው አቻቸው በዛሬው ዕለት በሲንጋፖር ተገናኝተው ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ኪም ጆንግ ኡን የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸውን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

ሁለቱ መሪዎች ያደረጉትን ውይይት አስመክልቶ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ይህ ነገር ብዙዎችን ያስደስታል፤ ምክንያቱም የሁለቱ ሀገሮች ጉዳይ ለዓለም ስጋት ነበር ሲሉ ብለዋል፡፡

የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን በበኩላቸው፥ ከፕሬዚዳንት ትራምፕ ጋር ያደረኩት ውይይት ታሪካዊ እና እዚህ ለመድረስም ብዙ ውጣ ውረዶች የታየበት ነው ሲሉ ነው የተናገሩት፡፡

ዘገባው የቢቢሲ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *