በየመን የባህር ዳርቻ 46 ዜጎቻችን ለህልፈት መዳረጋቸው መንግስት ማረጋገጫ ሰጠ፡፡

መንግስትበየመን የባህር ጠረፍ የደረሰን የጀልባ አደጋ አስመልክቶ ወደ ስፍራው ሰዎችን በማሰማራት፣ በአካባቢውየሚገኙ ኤምባሲዎቻችንን በማንቀሳቀስ እና የመን እና አዲስ አበባ የሚገኘው የዓለም አቀፍ የፍልሰት ድርጅት ጋርበመሆን አደጋውን በቅርበት ሲከታተለው እንደነበር አስታውቋል፡፡

በተደረገው ክትትልም 46 ያህል ዜጎቻችን በአሳዛኝ ሁኔታ ህይወታቸውን እንዳጡ አስታውቋል።

መንግስት ከተባበሩት መንግስታት የፍልሰት ድርጅት እንዲሁም ከአደጋው የተረፉ ወገኖች ጋር ባደረገው ክትትልም 100ያህል ኢትዮጵያውያንን የጫነች ጀልባ ከቦሳሶ ሶማሊያ ተነስታ ስትጓዝ ካደረች በኋላ ግንቦት 29 ቀን 2010 ዓ.ም የመንየባህር ጠረፍ ላይ ስትደርስ በደረሳባት አደጋ 46 ሰዎች ሲሰጥሙ 15 ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም ብሏል፡፡

ቀሪዎቹ ከአደጋው የተረፉ 39 ወገኖቻችን በአከባቢው የሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች እንዲሁም ከዓለም አቀፍየፍልሰት ድርጅት ጋር በመተባበር የመን ውስጥ የአስቸኳይ ጊዜ የህክምና ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው፡፡

በዚህ ጊዜ ይህን አሳዛኝ አደጋ መከሰቱ የህገ ወጥ ሰዎች ዝውውር እንቅስቃሴው ምን ያህል ውስብስብና አስቸጋሪ የወንጀል ድርጊት እንደሆነ በግልጽ የሚያሳይ ነው መንግስትም ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል ብሏል፡፡

ጀልባዋ የመስመጥ አደጋ የደረሰባት ከመጫን አቅሟ በላይ የሆነ ተሳፋሪ ይዛ በመጓዟ እና በዚህ ጉዞ ወቅትም ተሳፋሪዎቹከጸጥታ ሀይሎች እና ከሰው እይታ ለመራቅ በማሰብ ከየብስ አቅራቢያ ርቀው ይጓዙ ስለነበር የህይወት ማትረፍ ሙከራውውጤት እንዳላመጣ ከአለም አቀፍ አጋሮች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ሲል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አሰታውቋል ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *