ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ላይ የሚሰራው ቁጥጥር  አጠናክሮ እንደሚቀጥል የገቢዎች ሚኒስቴር ገለጸ

በሚኒስቴሩ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ አዲሱ ይርጋ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት በዚህ ሳምንት በአፋር ክልል ላይ 10 ሚሊየን ብር በአንድ የባንክ ሰራተኛ በመኪና ሊወጣ ሰል በቁጥጥር ስር መዋሉን አስታዉሰዋል፡፡

ይህ ብቻ አይደለም ህዳር 24 2011 ዓ.ም ከምሽቱ 6፡00 ላይ 6 ሺ170 ፓውንድ፣ 33ሺ115 ዩሮ፣1ሚሊየን 260 ሺ 4 975 የኢትዮጵያ ብር በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኛ አቀባይነት ወደ ቻይና ለምትሄድ ሴት በማቀባበል ሂደት ውስጥ በቦሌ ጉምሩክ እና በጸጥታ አካላት በተደረገው የጋራ ትብብር የኮንትሮባንድ ገንዘቦቹ መያዙም አውስተዋል፡፡

በህገወጥ የሚዘዋወሩ ገንዘቦች ይዘውት የሚመጡት መዘዝ ብዙ ነውና ይህም  የአስፈፃሚው አካል ስራ ብቻ ሳይሆን ማህበረሰቡ ይህን ዓይነት ድርጊት ሲመለከት ለፀጥታ ኣካል ጥቆማ እንዲሰጥም ሚኒስቴሩ ጥሪ አቅርቧል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *