በቻይና  እና አሜሪካ  የንግድ ልውውጥ  ቻይና ፈጣን የንግድ  እርምጃ  መዉሰዷን እንደምትቀጥል ተናግራለች፡፡

የቻይና ባለሥልጣናት ዝርዝር መረጃ ሳይሰጡ አሜሪካ  በንግድ ልውውጥ  ላይ ለምትወስናቸዉ ዉሳኔዎች በተቻለ ፍጥነት አፀፋዉን በመመለሳቸዉ  እንደሚተማመኑ ተናግረዋል፡፡

ቢቢሲ በድረ ገፁ እንዳስነበበዉ  ሁለቱም ሀገሮች በቢሊዮኖች የሚቆጠር ዶላርን አንዳቸው በሌላቸዉ  ሸቀጦች ላይ ተከታትለው ከበድ ያለ ታክስ በመጣል  የንግድ  ጦርነት ማካሄዳቸዉን ቀጥለዋል  ሲል ዘግቧል፡፡

በሳምንቱ መጨረሻ, በአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና በቻይናዉ ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ አርጀንቲና ላይ በተካሄደው የG20 ጉባኤ  ላይ ጊዚያዊ ስምምነት ቢያደርጉም የሁለቱ ሀገራት የንግድ ጦርነት ግነ ሊቆም እንዳልቻለ ታዉቋል፡፡

በሁለቱም ጎራዎች የሚወጡ መረጃዎች ልዩነቶች እየጨመሩ ሲሆን  በዚህ የንግድ ጦርነትም  ዋሺንግተን እና ቻይና እርስ በእርሳቸዉ የሚጥሉት  የታሪፍ ጭማሬ  የዓለምን ኢኮኖሚን እየጎዳዉ ነዉ ተብሏል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *