በአዳማ ከተማ 10ሺህ 200 የአሜሪካን ዶላር በቁጥጥር ሥር ዋለ

0
14

በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 10 ሺህ 200 የአሜሪካን ዶላር በአዳማ ከተማ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የከተማው ፖሊስ መመምሪያ አስታውቋል።

የመምሪያው የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ሳጅን ወርቅነሽ ገልሜቻ እንደገለጹት ዶላሩ በህገወጥ መንገድ በግለሰቦች ሲዘዋወር ትናንት ማታ 3፡30 ላይ ሕብረተሰቡ ባደረገው ጥቆማ ሊያዝ ችሏል።

ገንዘቡ የሰሌዳ ቁጥሩ 2-17781 (አ.አ) በሆነ የቤት አውቶሞቢል ተሽከርካሪ ተጭኖ ከአዳማ ወደ አዲስ አበባ ከተማ በፍጥነት በመጓዝ ላይ እያለ በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ ልዩ ስሙ “ናማልድ” በተባለ አካባቢ በቁጥጥር ስር ውሏል።

ከመኪናው ጋር በተያዙ ሁለት ግለሰቦች ላይ ፖሊስ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን ሳጅን ወርቅነሽ አመልክተዋል።

ህገወጥ የገንዘብ ዝውውሩን በተቀናጀ መልኩ ለመከላከልና ለመቆጣጠር ህብረተሰቡ እያደረገ ያለውን ትብብር እንዲቀጥል አሳስበዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here