በየጊዜው እያደገ  የመጣውን የኢትዮጵያና ጃፓን ግንኙነት ወደ ከፍተኛ ደረጃ ማሸጋገር እንደሚገባ ተገለጸ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ዶ/ር ማርቆስ ተክሌ የጃፓን ዓለምአቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (JICA) ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችን እንዲሁም የጃፓን ብሔራዊ የድህረ-ምረቃ የፓሊሲ ጥናት ተቋም (National Graduate Institute for Policy Studies ) ባልደረባ የሆኑትን ፕሮፌሰር ኬኒች ኦህኖን በትላንትናው  ዕለት በፅ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

በውይይቱ የጃፓን ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ውስጥ መዋዕለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ እያሳዩት ያለውን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣ ፍላጎት ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ በመለወጥ ለሁለቱ ሀገራት የጋራ ጥቅም ማዋል ይገባልም ተብሏል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታው፣ ፕሮፌሰር ኦህኖ የኢትዮጵያን መልካም ገፅታ በማስተዋወቅ እንዲሁም የጃፓን ባለሀብቶች ደግሞ በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ የሚሰጡትን ድጋፍም  እንዳደነቁ ተነግሯል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታው ፕሮፌሰሩ በጃይካ በኩል ለኢትዮጵያ ለሚያደርጉት የፓሊሲ ምክርና ድጋፍም እዳመሰገኑም ታውቋል፡፡

ፕሮፌሰሩ በበኩላቸው የጃፓን የመኪና አምራች ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ኢንቨስት የማድረግ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

የፓሊሲ ጥናት ተቋሙ እና ኤጀንሲው የኢትዮ-ጃፓን የኢንዱስትሪ ፓሊሲ ምክክር መድረክን በመደገፍ እንደሚታወቁ ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *