ትራምፕ አሁንም ማክሮንን በነገር መጎንተላቸውን ገፍተውበታል

ትራምፕ አሁንም ማክሮንን በነገር መጎንተላቸውን ገፍተውበታል ፤ የአሁኑ ርዕሳቸው ደግሞ በፈረንሳይ በነዳጅ ዘይት ላይ የተጣለውን ታክስ በመቃወም የተነሳው ሰልፍ ነው

የሮይተርስ ዘገባ እደሚያስነበብበው ትራምፕ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ኢማኑኤል ማክሮን እና የፓሪስ የተቃውሞ ሰልፈኞች እኔ ከሁለት ዓመት በፊት በደረስኩበት መደምደሚያ መስማማታቸው አስደስቶኛል ብለዋል ፡፡

ትራምፕ የ2015 በፓሪስ የተደረሰውን የአካባቢ ጥበቃ ስምምነት ሲተቹ ‹‹ የፓሪሱ ስምምነት ሃላፊነት የሚሰማቸው ሃገራት ላይ የሃይል ፍጆታን ዋጋ ሲንር አካባቢን ክፉኛ የሚበክሉትን ግን በቀላሉ ያልፋቸዋል ማለታቸው ይታወሳል ፡፡

ለሳምንታት የቆየውን የጎዳና ላይ ተቃውሞ ተከትሎ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ የፈረንሳዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤድዋርዶ ፊሊፕ በነዳጅ ዘይት ላይ ሊደረግ የታሰበውን የታክስ ጫማሪ ቢያንስ ለስድስት ወር እንዲዘገይ መወሰናቸው ይታወቃል ፡፡

ውሳኔው በማክሮን የ18 ወራት የስልጣን ዘመን የታየ ከፍተኛው የአቋም ለውጥ መሆኑም ተነግሮለታል ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *