ዛሬ ምሽት በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ እጅግ በጉጉት የሚጠበቅ ጨዋታ ይከናወናል

5 Dec by EthioFM

ዛሬ ምሽት በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ እጅግ በጉጉት የሚጠበቅ ጨዋታ ይከናወናል

ዛሬ ምሽት በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ እጅግ በጉጉት የሚጠበቅ ጨዋታ ይከናወናል ፡፡

የማንቸስተር ዩናይድ እና አርሰናል ጨዋታ ጆዜ ሞውሪንሆን ከኡናይ ኤምሬይ ያገናኛል ፡፡

ከተጫዋቾቻው ከፍተኛ ድጋፍ ያላቸው ስፔናዊ መልበሻ ክፍሉን መቆጣጠር ከተሳናቸው ፖርቱጋላዊ ይፋጠጣሉ ፡፡

የቀያይ ሰያጣናቱ ወቅታዊ ብቃት ሚያስመካ አይደለም ፡፡ መድፈኞቹግን በድንቅ ግስጋሴ ላይ ናቸው ፡፡

ምናልባት ለለንደኑ ክለብ ፈተና ይሆንበታል ተብሎ የሚጠቀሰው ወደ ኦልድ ትራፎርድ ተጉዞ አሸናፊ ከሆነ ከአስር ዓመት በላይ የተቆጠረ መሆኑ ነው ፡፡

ጨዋታውን አርሰናል ካሸነፈ ከመጀመሪያዎቹ አራት ቡድኖች አንዱ ሆኖ መቸረስ መቻሉን የሚያረጋግጥበት ይሆናል ፡፡

የጆዜ ሞውሪንሆን ፈተናም ያገዝፈዋል ፡፡ ምናልባትም ኤድ ዉድዋርድ ተተኪያቸውን ማፈላለግ እንዲጀምሩ ያስገድዳቸዋል ተብሏል ፡፡

ዩናይትድ የድል ከቀናው ግን በቀዮቹ ቤት ተስፋ ይፈነጥቃል ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *