የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ እና ቼልሲ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኒውካስልን ለመረከብ መቃረባቸው ተሰምቷል

5 Dec by EthioFM

የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ እና ቼልሲ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኒውካስልን ለመረከብ መቃረባቸው ተሰምቷል

የኒውካስሉ ባለቤት ማይክ አሽ በዚሁ ሳምንት ባደረጉት ቃለ ምልስ ከመቼውም ጊዜ በላይ ኒውካስል ወደ አዲስ ባለቤቶች የሚሸጋገርበት ጊዜ መቅረቡን ተናግረዋል ፡፡

ድርድሮች ወደ መጠናቅ መድረሳቸውንም መግለጻቸው ይታወሳል ፡፡

ምናልባትም አሽሊ ሊጠቁሙ የፈለጉት ከ ኬንዮንን ጋር ያደረጉትን ድርድር ሊሆን እንደሚችል ተነግሯል ፡፡

ኬንዮን በአሁኑ ወቅት ከአሜሪካው የፋይናንስ አማካሪ ተቋም ሮክፌለር ካፒታል ማኔጅመንት ጋር አብረው እየሰሩ እንደሆነ ይታወቃል ፡፡

ተቋሙ ጥያቄውን በይፋ ስለማቅረቡ ግን እስካሁን የተባለ ነገር የለም ፡፡ እንደተባለው ሽግግሩ የሚፈጸም ከሆነ ግን የጥሩ የዝውውር መስኮት ከመከፈቱ በፊት ቢሆን ቡድኑን ለማጠናከር እንደሚረዳ ተነግሯል ፡፡

የክለብ ባለቤቶች ሲቀያሩ ፕሪምየር ሊጉ አንዳንድ ሰነዶችን ለማዘዋወር እና ተገቢውን ሰነድ ለማጠናቅ ሁለት ሳምንት ሊፈጅበት እንደሚችል ተነግሯል ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *