የኢብራሂሞቪች ሚላንን የመቀላቀል ህልም ማብቃቱ ተሰምቷል

ዝላታን ኢብራሂሞቪች እና ሚላን ሲያደርጉት የነበረው ድርድር ሳይታሰብ መቋረጡን እና በኤል ኤ ጋላክሲ የመቆየት ዕድሉ መስፋቱ ተነግሯል ፡፡

ስፖርት ኢታሊያ እንደዘገበው ትላንት ምሽት ድርድሩ ያልተጠበቀ እክል አጋጥሞት ሁለቱም ወገኖች ሃሳባቸውን ለማንሳት ተገድደዋል ፡፡

እስከ ትላንት ድረስ ስውዲናዊውን በመጪው ጥር የዝውውር መስኮት በውሰት ወደ ጣሊያን ለማምጣት የሚቻልባቸው ዝርዝር ጉዳዮች እየታዩ ነበር ፡፡

ዛሬ ላይ ግን ሮሶኔሪዎች ቡድናቸውን ለማጠናከር ዓይናቸውን ወደ ሌላ ቦታ ለማማተር ተገድደዋል ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *