የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ካቢኔ በምእራብ ኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ ባጋጠመው የፀጥታ ችግር ዙሪያ ተወያየ

0
82

የክልሉ ካቢኔ ትናንት ባካሄደው 4ኛ መደበኛ ስብሰባው በሰላም ጉዳይ በተለይም  በምእራብ ኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ ባጋጠመው የፀጥታ ችግር ዙሪያ ተወያይቷል።

የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ  መንግስት  ካቢኔ  በወቅታዊ ሁኔታዎችና በሌሎች ጉዳዮች ላይ በመወያየት ውሳኔዎችን ማሳለፉን የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ  አስታውቋል፡፡

የክልሉ ብሄራዊ ክልላዊ  መንግስት ሰላምን ለማረጋገጥ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራም  ተገልጿል።

የሰው ህይወት መጥፋት እና የዜጎች መፈናቀል እንዲቆም ብሄራዊ የደህንነት ምክር ቤት ያሳለፈውን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ እንደሚደግፍ እና ስራ ላይ እንዲውል እንደሚሰራ ገልጿል።

የክልሉ ህዝብ የህግ የበላይነት እንዲከበር እና የሀገሪቱ ሰላም እንዲሰፍን እያቀረበ ባለው ጥያቄም  እርምጃዎች መውሰድ መጀመሩን እና እርምጃውም ተጠናክሮ  እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡

እስካሁን በተወሰደው እርምጃም በዜጎች ላይ አሰቃቂ ወንጀል የፈፀሙ ከ200 በላይ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን እና የቀሩትንም በቁጥጥር ስር በማዋል ለህግ የማቅረብ ስራ እንደሚሰራ ነው በመግለጫው የተገለጸው።

ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚደረገው ድጋፍም ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተጠቅሷል፡፡

የክልሉ መንግስት ካቢኔ የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ሰራተኞችን እንደ አዲስ ለመመደብ የቀረበ ረቂቅ የውሳኔ ሀሳብ ላይም ተወያይቶ አቅጣጫ አስቀምጧል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here