የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር 408 ኢትዮጵያውያንን ከየመን ወደ አገራቸው መለሰ

0
50

ሚኒስቴሩ ወደ ሳውዲ አረቢያ ሲጓዙ የመን ላይ ታስረው የነበሩ 408 ኢትዮጵያውያን ዜጎቻችንን ወደ አገራቸው መመለሱን አስታውቋል።

የዕርስ በርስ ጦርነት በሚካሄድበት የመን ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ወደ ሳውዲ አረቢያ ለመሄድ ሲሞክሩ ከነበሩት ውስጥ ህይወታቸው ለአደጋ ተጋልጦ የቆዩት ኢትዮጵያውያን የተመለሱት ባለፉት ቀናት በተደረገው ስራ ነው ተብሏል፡፡

ከተመለሱት 408 ዜጎች ውስጥ ሶስት መቶ የሚሆኑት ወንዶች፣ ቀሪዎቹ ደግሞ ሴቶች እንደሆኑም ተሰምቷል፡፡

ከተመለሱት መካከልም ጥብቅ የህክምና ክትትል የሚያስፈልጋቸው ሲሆኑ ተገቢውን የህክምና ድጋፍ እንዲያገኙ እየተደረገ ነው።

ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳገኘነው መረጃም ዜጎቻችንን ወደ አገር ለመመለስ የተቻለው ከዓለም አቀፍ የፍልሰት ተቋም (አይ.ኦ.ኤም) ፣ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ እንዲሁም ከኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳዮች ዋና መምሪያ ጋር በተሰራው ስራ እንደሆነ ገለጿል፡፡

በቀጣይነትም ሚኒስቴሩ ለዜጎች ደህንነት ትኩረት በመስጠት በመጪው ቀናት ከሳውዲ አረቢያ፣ ታንዛኒያ እና ከሊቢያ ዜጎቻችንን ወደ አገራቸው ለመመለስ የቅድመ ዝግጅት ስራ ተከናውኗል ብሏል።

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here