ደቡብ አፍሪካ የመጀመርያዋን ሴት አቃቢ ህግ ሾማለች

የሲሪል ራማፖሳ መንግስት በሀገሪቷ ታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ ሴት አቃቢ ህግ ሲሾሙ በደቡብ አፍሪካ የተንሰራፋዉን ከፍተኛ ሙስና ለመዋጋት ነዉ፡፡

የቀድሞዉን መሪ ጃኮብ ዙማን ጨምሮ ከፍተኛ ባለስልጣናት በሙስና ወንጀል ተዘፍቀዉ ለፍርድ አለመቅረባቸዉ የጠቅላይ አቃቢ ህጉ ቢሮ ችግር ተደርጎ ሲወሰድ ነበር፡፡

አዲስ የተመረጡት አቃቢ ህግ ወ/ሮ Shamila Batohiም ይሄንን ስህተት ለመቅረፍና ሙስናን በሀቅ ለመዋጋት ቃል ገብተዋል፡፡

ፕሬዘዳንት ራማፖሳ የአቃቢ ህጓ መመረጥ መንግስታችን የሀገሪቷን ዋነኛ ማነቆ የሆነዉን ሙስና ለመዋጋት ያለዉን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ሲሆን ከፍተኛ ባለስልጣናትም ከተጠያቂነት እንደማያመልጡ ማሳያ ነዉ ብለዉታል፡፡

ተመራጯ ጠ/አቃቢ ህግ Shamila በበኩላቸዉ ሀላፊነት የእሳት ወንበር ላይ እንደመቀመጥ ነዉ ሲሉ ገልፀዉታል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *