ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች የተሳተፉ አካላትን ለመለየት የምርመራ ቡድን ማሰማራቱን ጠቅላይ አቃቢ ህግ አስታወቀ

0
2

የፖበተደራጀ የኢኮኖሚ አሻጥር፣ሌብነትና፣ የሰብአዊ መብት ጥሰት የተሳተፉ ሕገ-ወጦችን ወደ ሕግ የማቅረቡ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል፡፡

አገሪቱ ያለችበትን ለውጥ ለማስቀጠል ህግ የማስከበሩ ስራ ይቀጥላል ብሏል በመግለጫው።

በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ሆን ብለው ግጭቶችን በቀሰቀሱ ፣ለዜጎች ሞት፣ መፈናቀልና ለንብረት መጥፋት መንስኤ የሆኑ አካላትን በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ ችግሩ በተከሰተባቸው ሰፍራዎች የተደራጀ የምርመራ ቡድን መላኩ ተገልጿል።

የምርመራ ውጤቱም በየጊዜው ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግም የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ ለኢትዮ ኤፍ በላከው መግለጫ አስታውቋል።

ህዝቡም ይህን እርምጃ በመደገፍና ከለውጡ ጎን በመሆን መንግስት እያካሄደ ያለውን የሕግና የፍትህ ማሻሻያ ስራ እንዲደግፍ ጥሪ ቀርቦለታል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here