የጥምቀት በዓልን በዩኔስኮ ዓለም አቀፍ ቅርስነት ለማስመዝገብ ጥረቶች እየተደረጉ ነው ተብሏል፡፡

በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚደረጉ የጥምቀት በዓል አከባበሮችን፣ ወደ መስህብነት ለመለወጥ ከወረዳዎች ጀምሮ እስከ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ድረስ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ነዉ፣ የባሕል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከፍተኛ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ካሳሁን አያሌው የተናገሩት፡፡

በሰሜን ሸዋ ምንጃር ሸንኮራ፣ በደቡብ ክልል ደራሼ፣ በትግራይ ክልል ማይጨው እና ሌሎች አካባቢዎች የበዓል አከባበሩን የማስተዋወቅ እና ጎብኝዎች እንዲታደሙ ሁኔታዎችን የማመቻቸት ሥራዎች መሠራታቸውንም ለአብነት ጠቅሰዋል፡፡

ከማይዳሰሱ ቅርሶች የሚመደበውን የጥምቀት በዓል በዩኔስኮ ዓለም አቀፍ ቅርስነት ለማስመዝገብ ጥረቶች እየተደረጉ ነዉም ብለዋል፡፡

በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት መመዝገቡ በዓሉ ዓለም አቀፍ ዕውቅናው እንዲጨምር እና የጎብኝዎች ፍሰት እንዲያሻቅብ ይረዳልም ነው ያሉት ባለሙያው፡፡

የጥምቀት በዓል ለቱሪዝሙ ዘርፍ ከፍተኛ ፋይዳ አለው›› ያሉት ባለሙያዉ፣ ሃይማኖታዊ ይዘቱን እና ፌስቲባሎችን እንዲሁም ትዕይንቶችን ለመታደም፣ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ጎብኝዎች እንደሚመጡም ነው የተናገሩት፡፡ ይህም ለሀገራችን ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ጠቀሜታ ያበረክታል ብለዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *