ፖሊስ በቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር አብዲ መሐመድ ኡመር ላይ ሲያደርግ የነበረውን ምርመራ ማጠናቀቁን አስታወቀ።

በአቶ አብዲ መሐመድ ኡመር መዝገብ እርሳቸውን ጨምሮ ሌሎች ሶስት ተጠርጣሪዎች ይገኛሉ።

ተጠርጣሪዎቹ ሐምሌ 2010 ዓ.ም በሶማሌ ክልል ተከስቶ በነበረው ሁከትና ብጥብጥ እጃቸው አለበት ተብለው በቁጥጥር ስር የዋሉ ናቸው።

አንደኛ ተጠርጣሪ አቶ አብዲ መሐመድ ኡመር፣ ሁለተኛ ተጠርጣሪ ወይዘሮ ራህማ መሐመድ፣ ሶስተኛ ተጠርጣሪ አቶ አብዱራዛቅ ሳኒ እና አራተኛ ተጠርጣሪ አቶ ፈርሃን ጣሂር በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ጉዳያቸው ሲታይ ቆይቷል።

ፖሊስም በግለሰቦቹ ላይ ምርመራ ሲያደርግ የቆየ ሲሆን ዛሬ ምርመራውን አጠናቅቆ መዝገቡን ለአቃቢ ህግ ማስረከቡን አስታውቋል።

የቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር በሰብአዊ መብት ጥሰት፣ የብሔርና የሃይማኖት ግጭት በማስነሳትና በሌሎችም ወንጀሎች ተጠርጥረው ከአምስት ወራት በፊት ነበር በቁጥጥር ስር የዋሉት።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *