በአገሪቱ የኤሌክትሪክ ሀይል ስርጭት በፈረቃ ሊደረግ ነው

ሰሞኑን በሀገር አቀፍ ደረጃ የተከሰተው የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ በግድቦች በቂ ውሀ ባለመኖሩ ምክንያት የተከሰተ እንደሆነ የኢፌዴሪ የውኃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ የኃይል መቆራረጡ የተከሰተው በተለይ በጊቤ 3 የሀይል ማመንጫ ግድብ በተከሰተው የዝናብ እጥረት ምክንያት የግድቡ ውሀ በመቀነሱ መሆኑን ነው የገለፀው፡፡

በአሁኑ ሰአት በአገሪቱ የ476 ሜጋ ዋት የሀይል እጥረት መከሰቱን የኢፌዴሪ የውኃ መስኖና ኢነርጂ ሚንስትር ዶ/ር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ አስታውቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለሱዳን እና ጅቡቲ ትልክ የነበረውን የኤሌክትሪክ ሀይል እንደምታቋርጥም ተገልጿል፡፡

አገሪቱ ከሀይል ሽያጩ ታገኝ የነበረው 180 ሚዮን ዶላር እንደነበርም ተገልጿል፡፡

በእጥረቱ ምክንያትም የኤሌክትሪክ ሀይል በመላ አገሪቱ በፈረቃ እንደሚሆን ሚንስትሩ ያስታወቁ ሲሆን ከፍተኛ ሀይል የሚጠቀሙ ድርጅቶችም የፈረቃው አካል ይሆናሉ ተብሏል፡፡

በቅርቡ በቂ ዝናብ የሚጥል ከሆነ ችግሩ ሊቃለል እንደሚችልም በመግለጫው ተጠቁሟል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *