414 ሚሊዮን ቁርጥራጭ ፕላስቲኮች በአውስትራሊያ ሞቃታማ የባህር ዳርቻወች ተገኙ

አንድ ሚሊዮን ጫማዎች እና 370 የጥርስ ቡሩሾች 414 ቁርጥራጭ ፕላስቲኮች በህንድ ውቅያኖስ አካባቢ ባለው ሞቃታማው Cocos መገኘቱን አዲስ ጥናት ማሳየቱን ሲኤን ኤ ዘግቧል፡፡

ጥናቱን ያሰራጨው ሳይንቲፊክ ሪፖርት መጽሔት እንዳለው በዚህ የአውስትራሊያ አካባቢ 238 ቶን የሚመዝን ፕላስቲክ አለ፡፡

የሚገርመው በዚህ ስፍራ የሚኖሩት ሰዎች ከ500 አይበልጡም፡፡

ጥናቱን ያደረገው ቡድን እንደሚለው ይህ ቆሻሻ መነሻው ከ27 የባህር ዳርቻዎች ነው፡፡

ከዚህ ስፍራ በ2ሺህ 750 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የቱሪስት ስፍራ አለ ፡፡

ከቆሻሻዎቹ መካከል ግለሰቦች የሚጠቀሟቸው የጥርስ ቡሩሾች ጫማዎች ይገኙበታል ተብሏል፡፡

የፕላስቲክ ብክለቶች ባህር ለሚኖሩም ሆነ ለሰው ልጅ በእጅጉ አደገኛ መሆናቸውን ጥናቱ አብሮ ገልጿል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *