ዛሬ የሰላም ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚል ይከፍቱታል ተብሎ የሚጠበቀው የኢድ ኤክስፖ እስኪጠናቀቅ የአፍጥር ስነ ስርአት ይኖረዋል ተባለ

ለ12 ተከታታይ ቀናት በሚቆየው የኢድ ኤክስፖ በ12ቱ ቀናትም ሀይማኖታዊ ስነ ስርዓቱን የጠበቀ የአፍጥር ስነ ስርዓት ይካሄዳል መባሉን ሰምተናል፡፡

ዛሬ በሚካሄደው የመክፈቻ ስነ ስርዓት ላይም የሰላም ሚስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል እንደሚገኙ ይጠበቃል ተብሏል፡፡

ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በትብብር የሚዘጋጀዉ 8ኛው የኢድ ኤክስፖ ከዛሬ ጀምሮ እሰከ ግንቦት 27 በኤግዚቢሽን ማዕከል ይካሄዳልም ተብሏል፡፡

የኢድ ኤክስፖ ሲካሄድ ማህበራዊ ሀላፊነትን ለመወጣት የሚያስችሉ ስራዎችም ጎን ለጎን እንደሚሰሩ የኢድ ኤክስፖ ፕሮጀክት አስተባባሪዉ ለኢትዮ ኤፍ ኤፍም ተናግረዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *