የፌደራል መንገድ ፈንድ ጽህፈት ቤት ባለፉት 9 ወራት ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ገለጸ

የጽህፈት ቤቱ ኮርፖሬት ኮሙንኬሽን ዳይሬክተር አቶ አስራት አሳለ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደገለጹት ባለፉት ዘጠኝ ወራት 2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር ገቢ ተሰብስቧል።

ገቢው የተሰበሰበው በነዳጅ  ላይ ከተጣለው የመንገድ ፈንድ ታሪፍ፣ በዘይትና ቅባት ላይ የተጣለው የመንገድ ፈንድ ታሪፍ፣ ከመንገድ ጠቀሜታ ገቢ፣ ከግምጃ ቤት ሠነድ ከሚገኝ ወለድ  እና ክብደትን መሠረት ያደረገ የመንገድ ፈንድ ዓመታዊ ተሽከርካሪ ማደሻ ክፍያዎች ነው።

ጽህፈት ቤቱ በተጠቀሰው ወራት ውስጥ 1 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ፣ 2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

በተመሳሳይ በ9 ወራት ውስጥ 1 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ለመንገድ ኤጀንሲዎች ክፍያ ለመፈጸም ታቅዶ 869 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር ክፍያ ተፈጽሟል፡፡

የመንገድ ኤጄንሲዎቹ በተባሉት ጊዜና ሁኔታ የክፊያ ማስረጃዎችን አለማቅረባቸው ለእቅዱ ማነስ ምክንያት ነው ተብሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *