ባለፉት 10 ወራት ከወጪ ንግድ የተገኘው ገቢ በ196 ሚሊዮን ዶላር ቅናሽ አሳየ

የንግድና ኢንዱሰትሪ ሚኒስቴር ለኢትዮ ኤፍ ኤም በበጀት ዓመቱ  አስር ወራት ውስጥ  ከግብርና፣ ከማኑፋክቸሪንግ እና ከማዕድን ምርቶች  ዘርፍ በአጠቃላይ  3 ነጥብ 51 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ  የተገኘው  2 ነጥብ 15 ቢሊዮን ዶላር ብቻ ነው፡፡

ገቢው ከ2010  በጀት ዓመት  ተመሳሳይ  ወራት ጋር ሲነፃፀር  በ 8 ነጥብ 38 በመቶ  ወይም የ196 ሚሊዮን ዶላር ቅናሽ አሳይቷል።

ከተያዘው ዕቅድ አንጻር በውጭ ምንዛሪ ገቢ ዝቅተኛ ገቢ ያስመዘገቡ የወጪ ንግድ ምርቶች ፤  ወተትና የወተትና ስጋ ተዋጽኦ ፣ ቆዳና የቆዳ  ውጤቶች፣ ቅመማቅመም፣ ዓሳ፣ ማር፣ ምግብ መጠጥና ፋርማቲስቲካል፣  ማዕድናት፣ የቁም እንሰሳት እና ብረታ ብረት ናቸው ተብሏል፡፡

የቅባት  እህሎች፣ ኤሌክትሪክ፣ ቡና፣ ጨርቃጨርቅና አልባሳት፣ አበባ፣ ሻይ ቅጠል፣ አትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች ለኢትዮጵያ የተሻለ ገቢ ያስገኙ ምርቶች ናቸው።

ዘገባው የባልደረባችን ዳንኤል መላኩ ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *