በኢትዮጵያ በየሳምቱ ከ300 በላይ ሰዎች በሲጋራ ምክንያት ህይወታቸውን ያጣሉ ተባለ።

በኢትዮጵያ የዓለም ትምባሆ የማይጨስበት ቀን እየተከበረ ይገኛል::
በአሁኑ ሰአት በዓለማችን ከ1.1 ቢልዮን በላይ ሲጋራ አጫሾች እንዳሉ የአለም ጤና ድርጅት መረጃ ይጠቁማል፡፡ከነዚህ ውስጥ 80 በመቶ የሚሆኑት ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሐገራት የሚኖሩ ናቸው።
በትንባሆ ጭስ ውስጥ ከ7ሺህ በላይ ኬሚካሎች እና ውህዶች እንደሚገኙ ተመራማሪዎች አረጋግጠዋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ 70 የሚሆኑት በተለየ መልኩ ለካንሰር የሚያጋልጡ ኬሚካሎች ናቸው፡፡
የትንባሆ ጭስ አምስት ሰዓት ለሚሆን ጊዜ በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በውስጡ የያዛቸው ኬሚካሎች ለሳንባ ካንሰር ዋነኛ መንስኤ ሲሆኑ ለሳንባ ነቀርሳ እና ለከፍተኛ ስር የሰደደ የመተንፈሻ አካላት በሽታ ተጋላጭነትንም ይጨምራሉ፡፡
በየዓመቱ በሲጋራ ማጨስ ምክንያት ሰባት ሚሊዮን ሰዎች የሚሞቱ ሲሆን አንድ ሚሊዮኖቹ ደግሞ ከአጫሾች በሚወጣው ጭስ ምክንያት ይሞታሉ።
Tobacco.org የተባለው ድርጅት ባስቀመጠው መረጃ መሰረት በኢትዮጲያ 18 ሺህ የሚሆኑ እድሜያቸው ከ10-14 ያሉ ልጆች እና 2.2 ሚልዮን የሚጠጉ ከ15 ዓመት በላይ የሆኑ አዋቂዎች በየቀኑ ሲጋራ እንደሚያጨሱ ይጠቁማል።
ይኸው ድርጅት ባወጣው መረጃ መሰረት በሐገራችን 238 የሚሆኑ ሲጋራ የሚያጨሱ ወንዶች እንዲሁም 65 የሚሆኑ ሴቶች በየሳምንቱ ይሞታሉ ይላል፡፡
በሀገር አቀፍ ደረጃ ትምባሆ እና የሳንባ ጤና በሚል መሪ ሀሳብ እየተከበረ ይገኛል፡፡

ዘገባው የሔኖክ ወ/ገብርኤል ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *