ኢትዮጵያ ከ2 ወር በፊት ያጸደቀችው የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጠና ስምምነት ወደ ተግባር መግባቱ ተገለጸ

31 May by Ethio

ኢትዮጵያ ከ2 ወር በፊት ያጸደቀችው የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጠና ስምምነት ወደ ተግባር መግባቱ ተገለጸ

ከሶስት ዓመት በፊት በሩዋንዳ ኪጋሊ የተረቀቀው የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጠና ስምምነትን ከ55 ሀገራት መካከል 52ቱ ፈርመዋል፡፡
ስምምነቱን ከፈረሙ አገራት መካከል 22 በአገራቸው የህግ አውጪ አካል ካጸደቁት ወደ ትግበራ ይቀየራል በሚለው መሰረት ስምምነቱ ከዛሬ ጀምሮ መተግበር መጀመሩን የአፍሪካ ህብረት በድረገጹ ይፋ አድርጓል። 
ይሁንና ስምምነቱ ሙሉ ለሙሉ የሚተገበረው ከአንድ ወር በኋላ በሚካሄደው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የመጨረሻ ውሳኔ ካሳለፉበት በኋላ ነው ተብሏል።
የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጠና ስምምነት አፍሪካዊያን በመካከላቸው ንግድ እና አገልግሎቶችን እንዲያቀላጥፉ፤ነፃ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ እና ሌሎችም የጋራ ጉዳዮች እንዲኖራቸው ያለመ ነው፡፡
አፍሪካን በንግድ የማስተሳሰሩ እንቅስቃሴ አህጉራዊ የጉምሩክ ማህበራት እንዲመሰረቱ ጭምር መንገድ እንደሚከፍትም ህብረቱ አስታውቋል፡፡

በሳሙኤል አባተ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *