ከ12 ሺህ በላይ ወጣቶችን የሚያሳትፍ የመስኖ እርሻ ፕሮጀክት ሊተገበር ነው።

ፕሮጀክቱ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተመረቁ ወጣቶች ወደ ዘመናዊ የመስኖ እርሻ እንዲገቡ የሚያበረታታ እንደሆነ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
ዘመናዊ የእርሻ ስራው 6 ቢሊየን ብር በሚጠጋ ተዘዋዋሪ ፈንድ የሚከናዎን ሲሆን በዚህ አመት ብቻ 12 ሺህ ወጣቶች ወደ ስራ ይገባሉ ተብሏል።
በመጀመሪያ ዙር ለሚሰማሩ ወጣቶችም 50 ሺህ ሄክታር መሬት መዘጋጀቱን የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ገልጸዋል።
የመስኖ እርሻው በ7 ክልሎች በሚገኙ 12 የመስኖ ግድቦች የሚለማ ሲሆን ወጣቶቹ በግብርና እና ተያያዥ ሙያዎች የሰለጠኑ ናቸው ብለዋል።
ተንዳሆ፣ አርጆ ዴዴሳ፣ ጊዳቦ፣ ኦሞ ኩራዝ፣ በለስ፣ ራያ ተፋሰስ፣ ሽንሌ ከርሰ ምድር፣ ኩለን፣ አሬቦ፣ ጎዴና አልዌሮ ወጣቶቹ የሚያለሙባቸው ፕሮጀክቶች ናቸው ተብሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *