ለኢድ አልፈጥር በአል ተብሎ የመብራት ፈረቃዉ እንደማይቀየር ተገለጸ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀዉ፤በሀይል እጥረት ምክንያት የፈረቃ አገልግሎቱ እንደበረ ይቀጥላል ብሏል።

የተቋሙ የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ መላኩ ታየ እንዳሉት በተፈጠረዉ የሀይል እጥረት ምክንያት ለበአሉ ሁሉን ህብረተሰብ ጋር መድረስ ስለማይቻል የፈረቃ አገልግሎቱ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

ይሁንና ከፍተኛ እና መካከለኛ የሀይል ተጠቃሚ ድርጅቶች ጋር ዛሬ ከሰዐት ምክክር ከተደገ በኋላ የሚለወጥ ነገር ካለ ለተጠቃሚዉ እናሳዉቃለን ብለዋል አቶ መላኩ፡፡

አሁን ባለዉ የሀይል አቅርቦት ግን ለሁሉም የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ በአንድ ጊዜ ማድረስ የአገሪቱ የሃይል አቅርቦት አቅም አይፈቅድም ብለዋል።

መንግስት የኤሌክትሪክ ማመንጫ ማዕከላት በገጠማቸዉ የዉሃ እጥረት ምክንያት እስከ ሰኔ 30 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ መብራት በፈረቃ ወደ ማከፋፈል እንተገባ ይታወሳል።

ዘገባው የአባቱ መረቀ ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *