ሪቻርሊሰን በኤቨርተን ደስተኛ መሆኑን ተናግሯል

3 Jun by EthioFM

ሪቻርሊሰን በኤቨርተን ደስተኛ መሆኑን ተናግሯል

ሪቻርሊሰን በኤቨርተን ደስተኛ መሆኑን ተናግሯል የኤቨርተኑ አጥቂ ሪቻርሊሰን በዚህ ክረምት ክለቡን ሊለቅቅ ይችላል የሚለው ሃሳብ ሲንሸራሸር መቆየቱ ይታወቃል ፡፡

ብራዚላዊው ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ እና ሊቨርፑል ሊያመራ እንደሚችልም ሲነገር ሰንብቷል ፡፡ በዚህ የውድድር ዘመን በአጥቂ መስመር በሁሉም ስፍራዎች ተሰልፎ 13 ጎሎችን ሲያስቆጥር አንድ ጎል የሆነ ኳስ አመቻችቶ አቀብሏል ፡፡

ባለፈው ክረምት ኤቨርተንን የተቀላቀለው የ22 ዓመት ተጫዋች በኤቨርተን ደስተኛ መሆኑን ተናግሯል ፡፡ በስራህ ስትመሰገን ደስ የሚል ስሜት ይፈጥርብሃል ፡፡ ነገር ግን በኤቨርተን ገና መደላደሌ ነው ፡፡ ደስተኛም ነኝ ብሏል ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *