ሳሪ ከቶተንሃም ተጫዋች ማስኮብለል ይፈልጋሉ

ሳሪ ከቶተንሃም ተጫዋች ማስኮብለል ይፈልጋሉ ተብሏል ማውሪዚዮ ሳሪ በቀጣዮቹ 48 ሰዓታት ውስጥ የጁቬንቱስ አሰልጣኝ ሆነው ሊሾሙ እንደሚችሉ ተነግሯል ፡፡

የመጀመሪያ ፈራሚያቸው ደግሞ የቶተንሃሙ ኪዬረን ትሪፒዬ ሊሆን እንደሚችል ተሰምቷል ፡፡ በጁቬንቱስም የሚፈለገው ተከላይ 35 ሚሊየን ፓውንድ ዋጋ ተቆርጦለታል ፡፡ ሳሪ ዩሮፓ ሊግን ባሸነፉ ከሰዓታት በኋላ ወደ ጣሊያን መብረራቸው ይታወቃል ፡፡

ከክለቡ ዳይሬክተር ማሪና ግራኖቭስኪያ ጋር ከተወያዩ በኋላ ቼልሲን መልቀቅ እንደሚፈልጉ ግልጽ አድርገዋል ተብሏል ፡፡ የ60 ዓመቱ አሰልጣኝ ከጁቬንቱሱ የስፖርት ዳይሬክተር ፋቢዮ ፓትሪቺ ጋር ዛሬ እንደሚወያዩም ተነግሯል ፡፡

የጣሊያኑ ክለብ ሳሪን በዓመት 6.2 ሚሊየን ፓውንድ እየከፈለ ለሶስት ዓመት ኮንትራት ሊያስፈርማቸው እንደሚችል እምነት አድሮበታል ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *