በአዲስ አበባ ባለፉት ሶስት ቀናት በተከሰቱ አራት አደጋዎች የሁለት ሰዎች ህይወት ጠፍቷል

የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለስልጣን እንዳስታወቀው ባለፉት ሶስት ቀናት ውስጥ በከተማዋ 4 አደጋዎች ተከስቷል ብሏል፡፡


የእሳት አደጋዎቹ የደረሱት በአዲስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 እህል በረንዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ እንዲሁም በአቃቂ ወረዳ 4 ያጋጠመ የመኖርያ ቤት ቃጠሎ ነበር፡፡


የሞት አደጋዎቹ ያጋጠሙት በንፋስ ስልክ ወረዳ ሰባት ላፍቶ ድልድይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሲሆን ሁለተኛ የሞት አደጋው የደረሰው ደግሞ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 አፍሪካ ትምህርት ቤት ጀርባ ነው፡፡ 


በዚህም ምክንያት የሁለት ሰው ሂወት ሲያልፍ ከሁለት መቶ ሺ ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወድማል ብለውናል የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለስልጣን የህዝብ ግኙኝነት ባለሙያው አቶ ንጋቱ ማሞ፡፡


ዘገባው የሄኖክ ወ/ገብርኤል ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *