በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በሰዓት ከ1 ሺህ በላይ የላብራቶሪ ምርመራዎችን ማካሄድ የሚያስችል ማሽን ተተከለ

በጥቁር አንበሳ አጠቃላይ አስፔሻላይዝ ሆፒታል ዛሬ የተመረቀው ይህ ማሽን በሰዓት ከ1000 በላይ የላባራቶሪ ምርመራዎች ማከናወን የሚችልና የሆስፒታሉን የላባራቶሪ የምርመራ አገልግሎት በእጥፍ ያሳድጋል ተብሏል።

ማሽኑ የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማንና ሌሎች እንግዶች በተገኙበት ተመርቋል።

መንግስት በሁሉም ሆስፒታሎች የላብራቶሪ ማሽኖችን ማሟላት ያስፈልጋል በሚል ባስቀመጠው እቅድ መሰረት ማሽኖችን በአገሪቱ በሚገኙ የተለያዩ ሆስፒታሎች በመትከል ላይ ይገኛል።


ዘገባው የዳንኤል መላኩ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *