የሞውሪንሆ የቻምፒየንስ ሊግ ምርጥ አስራ አንድ

ሞውሪንሆ በቻምፒየንስ ሊግ ምርጥ አስራ አንድ ውስጥ ስድስት የሊቨርፑል ተጫዋቾችን አካትተዋል ሊቨርፑል ቅዳሜ ለት ቶተንሃምን በማሸነፍ ዓምና በሚያሰቆጭ መንገድ ያመለጣቸውን ዋንጫ በእጃቸው ማስገባታቸው ይታወቃል ፡፡

ሆኖም በጆዜ ሞውሪንሆ የ2018/19 የቻምፒየንስ ሊግ ቡድን ውስጥ የተካተተው ብቸኛ የስፐርስ ተጫዋች ክርስቲያን ኤሪክሰን ብቻ ነው ፡፡ የቀድሞው የሪያል ማድሪድ አሰልጣኝ በቡድናቸው ውስጥ ያካተቱት ግማሽ ፍጻሜ እና ከዚያ በላይ መጓዝ ከቻሉ ቡድኖች ነው ፡፡

ስለሆነም ክርስቲያኖ ሮናልዶ በቡድኑ ውስጥ አልተካተተም ፡፡ ቫን ዳይክን ግን በተለየ መንገድ አወድሰውታል ፡፡ እርሱ ንጉስ ነው ፡፡ የትልቅ ስብዓና ባለቤት ነው ፡፡ በተለይ ቦታ አጠባበቁ ድንቅ ነው ብሏል ፡፡

በጆዜ ሞውሪንሆ ውስጥ የተካተቱት ተጫዋቾች

ግብ ጠባቂ ፡ አሊሰን ቤከር (ሊቨርፑል)

ቀኝ መስመር ተከላካይ ፡ ትሬንት አሌክሳንደር አርኖልድ ( ሊቨርፑል )

ግራ መስመር ተከላይ ፡ አንዲ ሮበርትሰን (ሊቨርፑል)

የመሃል ተከላካይ ፡ ቨርጂይል ቫን ዳይክ (ሊቨርፑል)

የመሃል ተከላካይ ፡ ማቲያስ ደ ሊት (አያክስ)

አማካይ ፡ ፍራንኪ ዲ ዮንግ (አያክስ)

አማካይ፡ ዶኒ ቫን ደ ቢክ (አያክስ)

አማካይ ፡ ክሪስቲያን ኤሪክሰን (ቶተንሃም)

አጥቂ፡ ሊዮኔል ሜሲ (ባርሴሎና)

አጥቂ ፡ ሳዲዮ ማኔ (ሊቨርፑል)

አጥቂ፡ ሞሃመድ ሳላህ (ሊቨርፑል)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *