የቡና እና መቐለ ጨዋታ በገለልተኛ ስታዲየም ይከናወናል

የቡና እና መቐለ ጨዋታ በገለልተኛ ስታዲየም ይከናወናል የኢትዮጵያ ቡና እና መቐለ 70 እንደርታ ጨዋታ አዳማ ላይ እንዲደረግ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ወስኗል።

ከ27ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መርሐ ግብር መካከል የኢትዮጵያ ቡና እና መቐለ 70 እንደርታ ጨዋታ ትላንት በአዲስ አበባ ስታዲየም መከናወን ሲገባው የፀጥታ ስጋት አለ በሚል ምክንያት አወዳዳሪው አካል ጨዋታውን መሰረዙ ይታወቃል።

ዛሬ ደግኞ የሊግ ኮሚቴው በወሰነው ውሳኔ መሠረት ጨዋታው ነገ (ማክሰኞ) በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም 09:00 ላይ በዝግ እንዲከናወን ተወስኗል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *