ጎትዘ ለዶርትሙን የልቀቁኝ ጥያቄ አለማቅረቡ ተሰምቷል

3 Jun by EthioFM

ጎትዘ ለዶርትሙን የልቀቁኝ ጥያቄ አለማቅረቡ ተሰምቷል

ጎትዘ ለዶርትሙን የልቀቁኝ ጥያቄ አለማቅረቡ ተሰምቷል ማሪዮ ጎትዘ የልቀቁኝ ጥያቄ አለማቅረቡን ያረጋገጡት የቦሩሲያ ዶርትሙንዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሃንስ ዮአኪም ቫትስከ ናቸው ፡፡

በኮንትራቱ ላይ አንድ ዓመት ብቻ የሚቀረው ጀርመናዊ ከአርሰናል ጋር ተያይዞ ስሙ ሲጠቀስ መቆየቱ ይታወቃል ፡፡ በቫትዝከ እምነት የዓለም ዋንጫ አሸናፊው ክለቡን ለመልቀቅ የሚፈልግበት ምን ምክንያት የለም ፡፡

ጎትዘ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በ26 የቡንደስሊጋ ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ ሰባት ጎሎችን ሲያስቆጥር ሰባት ጎል የሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *