በአዲስ አበባ ከኢድ አልፈጥር በአል ዋዜማ አንስቶ በደረሱ ሶስት አደጋዎች የሰው ህይወት ማለፉ ተገለጸ።

የከተማዋ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደገለጸው ትናንት በተከበረው ኢድ አልፈጠር በአል ዋዜማና በበአሉ እለት ሁለት የእሳት እንዲሁም አንድ የሞት አደጋዎች ተከሰተዋል፡፡

የሞት አደጋው የደረሰው በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ሽንት ቤት ተደርምሶ እድሜዋ 25 አመት የሆናት ወጣት ግለሰብ ላይ የደረሰ የሞት አደጋ ነው፡፡

የእሳት አደጋዎቹ የደረሱት ደግሞ በአራዳ ክፍለ ከተማ በወረዳ 10 ፒያሳ አካባቢ በሚገኙ የንግድ ሱቆች ላይ መድረሱ ተገልጿል።

በአደጋውም ግምቱ ሁለት ሚሊየን የሚሆን ንብረት ሲጠፋ 200 ሚሊየን የሚገመት ንብረት ደግሞ ከአደጋ ማዳን መቻሉን ኮሚሽኑ ገልጿል።

ሌላው የእሳት አደጋ የደረሰው በአዲስ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ልዩ ስሙ ሸማ ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኝው ሸማ ህንጻ ላይ ነው፡፡

በዚህ አደጋ ምክንያትም 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ሲወድም ሁለት ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ደግሞ ማዳን መቻሉ ተገልጿል።

የአደጋዎቹ መንስኤም በመጣራት ላይ ነው ተብሏል።

አደጋው ለመቆጣጠር በተደረገው ጥረትም በሁለት የድርጅቱ ስራተኞች ላይ ከባድ ጉዳት እንደደረሰ በኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ስለሺ ተስፋዬ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ የእሳት አደጋውን ለመቆጣጠር 130 ሺህ ሊትር ውሀ ጥቅም ላይ ማዋሉንም ገልጿል።

ዘገባው የሔኖክ ወ/ገብርኤል ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *