ትራምፕ ከኢራን ጋር ለመነጋገር ሁልጊዜም ዝግጁ ብሆንም ሁልጊዜም ግን ወታደራዊ እርምጃ ልንወስድ የምንችልበት ዕድሉ አለ ብለዋል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኢራን ፕሬዝዳንት ሃሰን ሩሃኒን ለማነጋገር ዝግጁ ነበርኩ ግን የአሜሪካ በእስላማዊ መንገስታት ላይ የሃይል እርምጃ የመውሰዷ ጉዳይ ሁልጊዜም እድሉ አለ ሲሉ ለሮይተርስ ተናግረዋል።

በመጀመርያ ወደ ስልጣን ስመጣ ኢራን እጅግ በጣም ጠበኛና ጠንቅ የሆነች ሃገር ነበረች፣ በአንደኛነት የምትቀመጥ ሽብርተኛ ሃገርም ነበረች፣ ምናልባት ዛሬም ነች፣ ብለዋል።


ትራምፕ አስፈላጊ ከሆነ ወታደራዊ እርምጃ ኢራን ላይ ሊወስዱ ይችላሉ ወይ ተብለው ተጠይቀው ፤ ሁሌም እድሉ አለ፣ ትፈልጋለህ ወይ ካላችሁ አልፈልግም ጦርነትን አልመርጥም ነው የምለው፣ ግን ሁልጊዜም የመፈጠር እድሉ አለ፡፡

ሩሃኒን ባናግራቸው ፣ ብንደራደር እመርጣለሁ ሲሉ ለሶሰት ቀናት ጉብኝት በለንደን የሚገኙት ፕሬዘዳንት ትራምፕ ለመገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል፡፡

በሔኖክ አስራት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *