የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት የነበሩት ዶ/ር ንጉሴ ምትኩ የኢቢሲ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ እያካሄደው ባለው መደበኛ ጉባኤ ዶክተር ንጉሴ ምትኩን የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) ዋና ስራ አስፈፃሚ አድርጎ ሾሟል፡፡

የቀድሞው የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ስዩም መኮንን በገዛ ፈቃዳቸው ሃላፊነታቸውን እንደለቀቁ ተገልጿል።

ሹመቱ በምክር ቤቱ አባላት አስተያየት ተሰጥቶበት በአራት ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ መጽደቁን ትግስት ዘላለም ዘግባለች።

ምክር ቤቱ ከሹመቱ በኋላ በሚኖረው ቆይታ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴርን የ11 ወራት አቅድ አፈጻጸም እንደሚገመግም ይጠበቃል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *