ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሱዳን ወታደራዊ ሀይልና ተቃዋሚዎችን ለማሸማገል ወደ ካርቱም ገቡ

በዳቦ ዋጋ መናር የተጀመረው የሱዳን ተቃውሞ ፕሬዘዳንት አልበሽርን ወደ አስር ቤት በማስገባት ብቻ አላቆመም።


ሱዳናዊያን ተቃውሟቸው ፍሬ አፍርቶ የቀድሞውን አስተዳደር ከስልጣን ቢያስነሳም ወታደራዊ ሀይሉ መልሶ ስልጣን መያዙ አበሳጭቷቸው በድጋሚ ለተቃውሞ ወደ አደባባይ አስወጥቷቸዋል።


እንደ አዲስ ተቃውሞ የተነሳበት የሱዳን ወታደራዊ ሃይል በሰልፈኞች ላይ ተኩስ በመክፈት ከ100 በላይ ሱዳናዊያን ሞተዋል።


በዚህ ምክንያትም በአገሪቱ አዲስ የፖለቲካ ውጥረት ተከስቷል።


ሱዳን ለምስራቅ፣ መካከለኛውና ሰሜን አፈሪካ መሸጋገሪያ አገር በመሆኗ ህገወጥ የሰዎችና የጦር መሳሪያ ዝውውር ወንጀሎችን እንዳያስፋፋ ተሰግቷል።


ጠቅላይ ሚኒስተር ዶክተር አብይ አህመድም እነዚህን ወገኖች ለማስማማት ዛሬ ማለዳ ካርቱም ገብተዋል።


ጠቅላይ ሚኒስትሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው፣የጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሰዓረ መኮንን፣የደህንነትና የጸጥታ ሃላፊዎችን አስከትለው ነው ወደ ሱዳን ያቀኑት። 


ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከማሸማገል በላፈ በኢትዮ ሱዳን ወቅታዊ ሁኔታዎች አንጻር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚወያዩ ይጠበቃል።


በሱዳን ተቃውሞ ከተቀሰቀሰ በኋላ ኢትዮጵያ በዚህ ዓመት ብቻ በተደጋጋሚ ወደ ካርቱም የዲፕሎማሲ ቡድን የላከች ሲሆን የአሁኑ ጉዞ ለ5ኛ ጊዜ ነው።

#PMOEthiopia

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *