ከውጪ የሚገቡ የሚረጉ የምግብ ዘይቶች በሰውነት ውስጥ የሚገኝን የስብ መጠን በመጨመር ለተለያዩ በሽታዎች እንደሚዳርጉ ተገለጸ

ከውጪ የሚገቡት የመርጋት ባህሪ ያላቸው ዘይቶች 50 በመቶ የሳቹሬትድ ፋት አሲድ ወይም ለኮሌስሮል መጠን መጨመር ተጋላጭ የሚያደርግ የአሲድ መጠን እንዳላቸው ተነግሯል።

የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሚረጉ የምግብ ዘይቶችን መመገብ ስለሚያስከትሉት ጉዳቶች ያጠናውን ጥናት ይፋ አደርጓል።

የኢንስቲትዩቱ ዳይሬክተር ዶ/ር ኤባ አባተ እንዳሉት ኢትዮጵያ ከውጪ የምታስገባው የምግብ ዘይት 81 በመቶ የሚሆኑት የፓልም ዘይቶችን ሲሆን ለነዚህ ዘይቶችም ከ8 እስከ 9 ቢሊየን ብር ፈሰስ ታደርጋለች።

ነገር ግን የእነዚህ ዘይቶችን ምርት ለረጅም ግዜ መጠቀም በሳቹሬትድ ፋት አሲድ ወይም ለከፍተኛ የኮሌስትሮን መጠን መብዛት ተጋላጭ ይደርጋሉ።

ይህ ደግሞ እንደካንሰር ና ሌሎች ተላላፊ ላልሆኑ ህመሞች እንደሚያጋልጥ ተጠቁሟል።
የሀገር ዉስጥ የምግብ ዘይት ምርቶችን ጥናቱ ያካቱተ ሲሆን በሀገር ውስጥ የሚመረቱ የምግብ ዘይቶች የአመራረት ሂደታቸው ላይ የጥራት ችግር አለባቸው።
መቼ ይመረቱ መች የአገልግሎት ግዜአቸው ያብቃ አይታወቅም ከጤና አኳያ ግን ይህ ነው የሚባል የጤና እክል አልፈጠሩም ትብሏል።

የፖልም ዘይት ህብረተሰቡ የሚጠቀመውን የምግብ ዘይት 81 በመቶ በመያዙ ጥናቱ ለጠቅላይ ሚንስትር ቢሮ ተልኮ ንግድና ኢንድስትሪ ሚንስቴር ቢሮ የተሻሉ የአማራጭ ሀሳቦችን እንዲያቀርብ ትዕዛዝ ተላልፏል ተብሏል።

ከከትሞች መስፋት ና ከህዝብ ቁጥር መጨመር ጋር ተያይዞ የሚረጉ የዘይት ምርቶችን የመጠቀም ፍላጎት ከፈረንጆቹ 2012 እስከ 2017 ከ 270ሺ ወደ 450 ሺ ሜትሪክ ቶን ያደገ ሲሆን በ2018 በአማካኝ የፍላጎት መጠኑ ወደ 600 ሺህ ሜትሪክ ቶን እንዳደገም ተገልጿል።

ዘገባው የትግስት ዘላለም ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *